ለተከበራችሁ የኢትዮ ላዮን አሲምባ ደብተራዉ የህዋ ሰሌዳ አዘጋጆች የአስተዳደር ጥያቄ አቤቱታ።

ከጌታቸዉ ረዳ (http://ethiopiansemay.blogspot.com)

አቤቱታዉ በቋሚነት በየጊዜዉ በድረገጻችሁ “ኦቦ አራዳ ሻዉል” (Obo Arada Shawl) በሚል የብዕር ስም ስለሚጽፈዉ ኤርትራዊዉ “ራስ ሃይሉ” መጠርያ ስሙ “ተወልደ” የተባለዉ ግለሰብ ነዉ። ግለ ሰቡ በእድሜዉ ወደ 70ኛዉ አመቱ የተጠጋ አዛዉንት ቢሆኑም፤ በጸረ ኢትዮጵያነቱ ለአንድነት በሚታገሉ እወቅ ኢትዮጵያዉያን ታጋዮች በእነ እንጂነር ሃይሉ ሻዉል፤ በእነ ዶ/ታ ወልደሰማያት፤ በእነ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ፤ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን እና በጣም በርካታ እወቅ በሆኑ በሞት የተለዩ ጀግኖች ጥንት ኢትዮጵያዉያን አርበኞች ሳይቀር ስም በመለጠፍ እና በማንኳሰስ በተለያዩ ፎረሞች እና በሰሌዳችሁ ላይም የኢሕአፓ ደጋፊ አባል ወይንም የአመራር አባል በሚያስመስለዉ አቀራረቡ በተለይም የኢሕአፓዉ “የጸጋየ ደብተራዉ” ስም በየጊዜዉ በመጥራት ለጸረ ኢትዮጵያ ተልእኮዉ በመጠቀም ኢትዮጵያዊ ጸሃፊ ለመመስል ኢትዮጵያዉያን እና የኢሕአፓ አባላትን በጣም በተካነ አቀራረብ በማሞኘት ጸረ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያስተጋባ ቆይቷል። ይግረማችሁ ብሎ ደግሞ በቅርቡ የኦነግ ወታደሮች አዛዉንት እና ህጻነት አማራ እና ትገሬ ገዳዮች መሆናቸዉ በሰነድ ተሰንዶ እያለ የነጻነት እና የዲሞክራሲ ታጋዮች ናቸዉ። ማለቱን ተያይዞታል።

በግሌ የሰዉየን ማንነት እና አጻጻፍ ከተጠራጠርኩ ቆይቻለሁ።ብዙዎቹ ግን የነቁበት አልመሰለኝም። ሰዉየዉ በፕሮፈሰር አለሜ እሸቴ (Opne letter to Professor Aleme Eshete the Crisis and the deportation of Hagos G/Yesus)) እና በእዉቁ ምሁር በፕሮፌሰር ሓጎስ ገ/የሱስ ላይ የሰነዘረዉ ጽሁፍ (በአሲምባ እና በማህደር ሰሌዳ ላይ) ተመልክቼ በዉይይት ፎረማችሁ ላይ ባቀረበዉ ጽሁፍ አስተያየቴን ስሰጥ እንደተለመደዉ የኦሮሞ ነጸነት ግምባር ብሎ ራሱን የሚያታልለዉ ወንጀለኛዉ “ኦነግ”ን በመደገፍ የጻፋቸዉን መልክቶቹ ለእናንተ እና ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን አንባቢዎች እንድታነብቡት ከዚህ ቀጥየ አቀርበዋለሁ ። ጽሁፉ በአሲምባ.ኦርግ ወይንም በደብተራዉ.ካም የሃሳብ መለዋጫ ሰሌዳ ላይ የጻፈዉ ቅጅ ነዉ።

On January 2, 2009 at 5:32 am obo arada shawl Said

To Getachew:-You should accept that you are not alone to born out of two nationalities or nations. Geta plus Redaie i.e Lord and Helper don’t match. What a confusion! You cannot be a master and a servant at the same time. Or you should give us a separate explanation GETA for who or SERVANT for whom? I am sure you are not a master to OLF or a servant to ePLF. After the Revolution of 1974 and which is still going on, you seem to be lost in the 18th Century. I am so sorry for you. Please, open your heart for solutions not for problems. I suggest you start by learning the ABC of DEMOCRACIA. I see that YOU and EPLF/TPLF army boast of 18,000 OLF soldiers were captured. The 18,000 were not soldiers of dictatorship but soldiers of DEMOCRACIA.

I just want to remind you that the OLH leadership chose to accept for four posts of a) Agriculture b) Education c) Development and d) Information. This is not difficult to figure out how smart the OLF leaders were. Mind you, they did not want to share power from the Defense, Foreign or Trade. They were looking for long term what we call DEMOCRACIA -building a bridge not destroying a bridge. Ato Getachew in any obituaries, you will see names, names and strange names. Lastly, what does Ras Hailu mean? Please, explain to me. I want to learn. I would suggest that you read my article entitled ” call me by my address, solutions with DEBTERAW, III” dated on October 23, 2008. I think it will indicate who we are first and then build a United States of AETHIOPIA (USAE)or something of that sort. Ato Germame Neway thinks that it is loaded and he does not believe it is appropriate to discuss with what he calls his “enemies”. And I am a believer who discusses with my enemies more than with my friends.

እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ኦነግ አገሪቱን ከወያኔ በበለጠ የጦር ሃይሉን የማንቀሳቀስ አቅሙ እንደሌለዉ ሁላችን ብናዉቀዉም፦ የተወልደ (“የኦቦ አራዳ ሻዉል”)- *ኦነግ* አስተዳደሩን የሲቭል አና የትምህርት ዘርፎችን ለመምራት የጓጓዉ አማርኛን እና የግዕዝ ፊደላችነን ለማጥፋት በቅኝ ገዢዎች ፊደል “የላቲን” ቋንቋ ለመተካት ሆን ብሎ እንደተሟሟተበት እና የልቡ እንዳደረሰለት እየታወቀ “ኦቦ ኣራዳ ሻዉል” ተባለዉ ጸረ ኢትዮጵያ ግለሰብ ግን ከላይ እንደጻፈዉ “ኦነግ የተረከበዉን ያስተዳደር ዘርፎች “ዲሞክራሲያ” ለመገንባት እና ሰላም ፈላጊ እና ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት እንጂ የጦር ሰዉ ቢሆን “የወያኔዉን የመከላከያዉ ሃይል በመቆጣጠር ያዝዘዉ ነበር” ሲል ሊነግረን ሞክሯል። ሞኝን ሞኝ ቢሉት ሹመት ይመስለዋል። ሰዉየዉ “ብልጣብልጥ-ሞኝ” መሆኑን እያወቅነዉ “ሞኝ” ብንለዉ – “ሹመት” ይመስለዋል እና እንቀጥል።

ወያኔ የማረካቸዉ/ (በሽግግሩ ጊዜ የበተናቸዉ 18,000 የኦነግ ታጣቂ) በሌንጮ ለታ እና በሌሎቹ ጸረ-ኢትዮጵያ ግለሰዎች የሚመራዉ የኦነግ ታጣቂ ሰራዊት በኦሮሞ የኢትዮጵያ ክፍላተሃገሮች (አሱ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፈ “ኤ’’ ኢትዮጵያ ይለዋል) ’አካባቢ የአማራዉን፤የትግራዩን እና የጉራጌ ገበሬዎች እና የሰፈራ ጣብያዎች ህጻናት ሳይቀሩ በአንድነት/በጀምላ ሰብስቦ በእሳት የጋዩት በእነዚህ በኦነግ ጦር መሆኑን እየታወቀ እና ሰብአዊ ተመጓቾች የዘገቡት “የዘር ማጥፋት” ወንጀል የተፈጸመዉ በዚህ በኦነግ ጦር እንደሆነ እየታወቀ- ግለሰቡ/(Obo Arada Shawl) ወንጀለኛዉን የኦነግ ጦር 18,000 OLF soldiers were captured. The 18,000 were not soldiers of dictatorship but soldiers of DEMOCRACIA. በማለት ሲከራከር- የኦነግ ጸረ ኢትዮጵያነት እኛ ብቻ ሳንሆን መሪዎቹ በቅረቡ “በተሳሳተ መንገድ ህዝቡን ይዋሹት” እንደነበረ አምነዋል። ይህ ግለሰብ የማንነቱ መለያ ቁልጭ ባለ መንገድ ሲነግረን _ እናንተ ወንድሞቼ ከእንግዲህ ወዲህ በመድረካችሁ ብታስተናግዱት እኔ ለድረ-ገጻችሁ የነበረኝን ከበሬታ እንዳለ ሆኖ “በናንተ ድረ ገጽ ግን እንደማልሳተፍ ግልጽ ላደርግላችሁ እወዳለሁ። ሰዉየዉን ብታስተናግዱት አንባቢ ለናንተ የነበረዉ ከበሬታ እንደሚቀንሰዉም በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።በተለይም ይህ ግለሰብ መድረካችሁን ለመጠቀም የኢሕአፓን ስም እና ታጋዮች ጣልቃ እያስገባ የጸረ አንደነቱን መልእክት ስለሚያስተጋባ ኢሕአፓዎች ለድረገጽ አዘጋጆቹ ብታሳስቡዋቸዉ ለድረጅታችሁ ክብር እና ስም ለመጠበቅ ያመቻችሗል።

ክቡራን ወገኖቼ ሆይ፦ እንደምታዉቁት ጌታቸዉ ረዳ በትግሬነቴ ብቻ ሳይሆን በ ኢትዮጵያዊነቴ እድሜየ በሙሉ የኮራሁበት አገሬ ኢትዮጵያ መሆኑን ታዉቃላችሁ። በ ኢትዮጵያዊነት እና ለኢትኦጵያ በመቆሜ ብዙ በጣም ብዙ በርካታ ጠላቶች አፍርቻለሁ።አገርን በመጨቆን ላይ ያሉት ብዙ የጥንት ወዳጆቼም በዚህ ፖለቲካ ሳቢያ ተለይቻቸዋለሁ። ያ ተነሳሁበት ኢትዮጵያዊነት ግቡ አስከ መታ እና አገሬ በነጻነት አስኮነረች ድረስ የጠላቶች ጉራ እና ዛቻ ከቶዉንም አልበገረኝም ለወደፊቱም አይበግረኝም።ከመጤፍም የምቆጥረዉ አይደለም። የወያኔ ጀሌዎች፤የሻዕቢያ ጀሌዎች የኦነግ ጀሌዎች “ጌታቸዉ” የሚለዉ የኢትዮጵያ ስም ሆነ የአማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት በተለያዩ ጊዜያት “በዘፈንም፤በጽሁፋቸዉም፤በንግግራቸዉም፤በትያትርም” የቻሉትን ያህል የአማራን ስም ለማንኳሰስ ብዙ- እጀግ ብዙ ጥረዋል።ግን ኢትዮጵያዊነትን መስበር አልቻሉም።

አሁንም ከላይ እንዳነበባችሁት በኢትዮጵያዉያን ወላጆቼ የተሰጠኝን መጠርያ ስሜ እና የወላጆቼን መጠርያ ስም በዚህ ዘረኛ ግለሰብ ሲያንኳሰስ እና ሲናናቅ በማንበቤ የማዝነዉ እኔ ሳልሆን በእኔ እና በወላጆቼ ስም በመቀለዱ እናንተ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ምንኛ እንደሚሰማችሁ እርግጠና ነኝ። እኔ እማ ዘረኛነቱንም ዘለፋዉንም እደሜየ ሙሉ በእነ ተወልደ ዓይነቱ የኤርትራ ዘረኞች፤ በላያችን ላይ ለብዙ አመታት ስለወረደብን ለምጀዋለሁ። የዘረኖች ጫጫታ አዲስ አይሆንብኝም። የሚያሳዝነዉ ግን የተለያዩ ስሞች የያዙ ራሳቸዉን መከላከል የማይችሉ ህጻናት እና በቀላሉ የሚሰበር ልብ የያዩዙ ጎልማሳ ሴቶች እና ወንዶች “የ አማርኛ ስማ በመያዛቸዉ ብቻ” በምን የሕሊና ስቃይ እየተራመዱ እንደሆነ የምታጡት አይመስለኝም።

ቀለም ቀመስ ሙሑራን ምንኛ በዘር ፖለቲካ ተዘፍቀዉ የራስ ቂልነታቸዉ ላልተማረዉ ህብረተሰብ እያንጸባረቁ እንደሆነ ከእናንተ የሚሰወር አይመስለኝም። (የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወደየት የሚለዉ የዘረኛዉ የአንዳረካቸዉ መጽሃፍ ምንኛ ሕዝቡ እንደበከለዉ ዉጤቱ ተምሬአለሁ በሚለዉ “ኦቦ አራዳ ሻዉል” በተባለዉ ዘረኛዉ ኤርትራዊ ወልዱ ተወለደ የዘረኝነት ምርቱ እያፈሰዉ መሆኑን ማየት ይቻላል።

To Getachew:-You should accept that you are not alone to born out of two nationalities or nations. Geta plus Redaie i.e Lord and Helper don’t match. What a confusion! You cannot be a master and a servant at the same time. Or you should give us a separate explanation GETA for who or SERVANT for whom?

ወንድሞቼ- ዘረኛዉ ኤርትራዊ “ራስ ሃይሉ” የብዕር ስሙ “አቦ አራዳ ሻዉል የተባለዉ ከላይ የተጠቀሰዉ ግለሰብ – በእኔ እና በወላጆጄ እንዲሁም በአያቶቼ ቅድመ ቅደመ አያቶቼ እና አያቶቹ ሲገለገሉበት የቆዉ ኢትዮጵያዊ ስም (what a confussion!በማለት የራሱን አዛዉንታዊ ኩታራ ጨንቅላት ሊገልጽ ሞክሯል) ወላጆቼ ስም ስያወጡልኝ ወይንም አያቶቼ የወላጆቼን ስም ስያወጡላቸዉ “ግራ አልተጋቡም”። ስም ሲወጣላቸዉ እና ስም ሲያወጡልኝ የማንንም ዘረኛ ፈቃድ አላስፈለጋቸዉም ነበር።ለዘረኞች የሚንበረከኩም አልነበሩም።የኢትዮጵያን ጀግኖች እየመሩ በጣልያን እና በድርቡሽ በሁለተኛ እና በመካከለኛ ደረጃ አዋጊ ጀኔራሎች ሆነዉ የድረቡሽን ምሽግ የበረገዱ ሁለቱም አያቶቼ ማንም ዘረኛ ደፍሮ ስምህ ለዉጥ ወይንም ስምህ አላማረንም ብሎ ከፊታቸዉ የሞከረ ፍጡር አልሰማንም። የሱ አያቶችም ከአያቶቼ ግምባር ፊት ቆመዉ ደፍረዉ ስምዎትን እና ማዕረግዎን ስም ይለዉጡ ብለዉ ይሞክሩት ነበር ብየም አልገምተዉም። አያቶቹ አንደ አያቶቼ የተከበሩ ጨዋ ኢትዮጵያዉያን ነበሩ የሚል ግምት ስላለኝ።ትናንት ከትናንት በስቲያ ለዘረኞች እና ለወራሪዎች ለታሪክ አፍራሾች ያልተንበረከኩት አያቶቼ በእኔ ዘንድ ሲደርስ የእኔ ስም እና የወላጆቼን “ስም ሲያነብቡ” “የማይጥማቸዉ” የዛሬ የዘመናችን ዘረኞች አነሱ በሚፈቅዱልኝና በሚመርጡልኝ ስም እንደማልጠራ በድጋሚ ዘረኞች እንዲያወቁት ላረጋግጥ።

ኢትዮጵያዉያን ወላጆቻችሁ የሰጡዋችሁን ስም አላማረንም እያሉ በዘረኝነት ጨዋታ እየገቡ በሌላ በኩል ደግሞ “ስለ ሕዝብ ጉዳይ እና ስለ ፖለቲካ” ላዉራ እና ልጻፍ እያሉ በ አደባባይ የኢትዮጵያዊነት ስም እና ኢትዮጵያን አርበኞችን ሲኮንኑ እና ሲያናንቁ ካሁን በፊት ያነበብናቸዉ ዘረኞች ከእኔም ሆነ ከሌሎች ኢትዮጵያ ታጋዮች ጋር ሲከራከሩ ፦ በዘር በሽታ በመለከፋቸዉ ወይንም ትላልቅ ዕዉቅ ሲቪክ ማሕበራት የመምህራን ማህበራትን በሚመሩ ታጋይ መሪዎች ላይ የማይገባ የዉርደት ዘለፋ ሲዘልፏቸዉ ተደምጠዉ በራሳቸዉ ቅሌት ፈጣን ዉድቀት እየጋበዙ ከመድረኩ ተሎ እንዴት ይወገዱ እንደነበሩ ሁላችሁም የምታስታዉሱት የቅርብ የኢንተርኔት ሰሌዳዎች ትዉስታ ነዉ። ይሄኛዉም በጸረ ኢትዮጵያዊነቱ እና በዘረኛነት አቋሙ ከመድረካችሁ በማስወገድ የአስተዳደር እርምጃ እንደምትወስዱበት አደራየ የጸና ነዉ።ድረ ገጸቻችሁ የ እነኒህ ግለሰቦች ማጀብ ከቀጠለ ግን እጣዉ እነሱን ሚከተል ይመስለኛል።

እስኪ ይሄነን አሱ አምርሮ የሚጠላዉ የትግራይ ሕዝብ እና ከትግራይ ሕዝብ አስበልጦ የሚወድደዉ የኦሮሞ ሕዝብ በማወዳደር ትግራይን Biologically/naturally “ስልጣን ናፋቂ፤የስልጣን ስስታም፤አወተሪታቲቭ/ጨቋኝ፤ገዳይ ፈላጭ ቆራጭ ያለዉን እና የኦሮሞ ሕዝብ ግን Biologically/naturally born Democrat ያለዉን ዘረኝነቱን እና ቂልነቱን አንብቡልኝ።<<1. OUR VISION: Germame & Getachew are in the business of “ETHIOPIA WILL PREVAIL>> <<I am in the business of “TRUTH WILL PREVAIL”. ይህ ያትዮጵያ አርበኞች እና የመጽሃፍ ቅዱሳችን መፈክር ከ እዉነት የራቀ መፈክር በማስመሰል መርሆአችንን በማንኳሰስ “ኢትዮጵያ” -ዉሸት”- ሆና “ በ ኢትዮጵያ ቦታ የተካዉ “ትሩዝ” ዊል ፕሪቨይል” ብሎታል። ኢትዮጵያ እና ዉሸት አንድ አድርጎ “ዕዉነት” በሚለዉ ተክቶባታል። ኢድየም/ቅኔኞች የምታዉቁት ይመስለኛል። የመለስ ዜናዊ ቅኔ ተመልሶ ዞሮ በ እነዚህ ዌብሳይቶች በግልጽ መነገር መጀመሩ ነዉ። አንድ በሉልኝ።

እኔ ከ አንድ የኦነግ አጃቢ ጋር ስለ ኢትዮያዊነት ስከራከር እኔኑን “ቅማላም ትገሬ” በማለት ወደ ችጋራምዋ ትገሬ ከአገራችን ወደ መጣችሁበት እነመልሳችሗለን ሲል (ትግሬዎችን ለማስወጣት የሚተባበሩት ሃኢሎች ደግሞ- አማሮች ኦሮሞዎች ናቸዉ ይላል) አንድ ኦነግ እነዲህ በማለት ሲጽፍልኝ አንብቡ እና (ኦቦ አራዳ ሻዉል- ‘አቶ ወልዱ ተወልደ) ደግሞ አሱን በመደግፍ ምን እንዳለ ይሄን ካነበባቸወሁ በሗላ ተመልከቱት።

የኦነጉን ሰዉየ ጸወሁፍ <<Just a question: did one OL…እዚህ ላይ የብልግና ቃላቶች ለሚዲያዉ ጥራት ሰርዠዋለሁ….። like it or not, you will be back to Meqele for Qulquwal-leqema. Till then enjoy Oromia’s meat, coffee and milk for you will never get it when the time comes. You and your poor future generation will have no chance to BEG in Oromia leave alone to brag like you are doing now.

<<leave alone Ob Arada. Go on and paint OLF further with your verbal SEGERA?>>

የሚቀጥለዉን ለ ኦነጉ ጀሌ በድጋፍ የጻፈዉ ደግሞ ያንብቡት።<<Helping the Tigrians or the Oromians is not bad thing after all. It is only the way you do it. I can understand both of your pains and struggle. Getachew’s disadvantage is that he was born in authoritative community whereas Fayyis’s advantage is because he came from democratic culture. The end result is that Getachew’s community has used their dictatorial nature for power whereas the Fayyis community are using their democratic nature ነዉ። አንድ በሉልኝ።

እንግዲህ ከዲሞክራቲክ ማህበረስብ የተወለደዉ ተወልደ እየመሰከረለት ያለዉ የኦነጉ ጀሌ ዲሞክራሲያዊ ጽሁፍ ከላኢ ተመልክታችሁታል። አቶ ተወልደ ህዝብን በዘር ፈጀ የኦነግ ሰረዊት እና አመራር አስከ እነ ፖሊሲዉ የመደገፉ መብቱ ነዉ። ህዝቡን እያወደዳደረ ትግሬዎችን በተፈጥሮ ስልጣን ዩሰኞች እና ፈላች ቆራጮች ማድረጉ ግን ከትብቅና አልፎ “ዘረኝነትን በሚዲያ ማንጸባረቁ” ኢትዮያዉን የሚወዱለት አይመስለኝም። ድረ ገጸች ይህነን ሲያነቡ ሰዉየዉን ማስወገድ ነበረባቸዉ።

የኦሮሞ ሕበረተሰብም ሆነ የትግራይ ህብረተሰብ በታሪካቸዉ ዲሞክራሲ የሚባል አሰራር እንዳልነበራቸዉ እና ሴቶችን የሚበድል መጮቆን (ጾታ) ቀለምም (ቆዳ) ሆነ ለዕድሜ ብቃት ወይንም (የወንድ ብልትን በመስለብ ለስልጣን/ለትዳር ብቁነት ማስመስከርን) ለስልጠን በግድያ እና ሕብረተሰብን በ ሌላዉ ህብረተሰብ ንበረት እና ቤተሰብ አመጽ እና ዘረፋ መሰማራትን፤ በተወሰኑ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩትን መዝለፍ/ለጋብቻ መከልከል….የመሳሰሉ ሰዉን እና ሕብረተሰብን የሚለያይ ስርዓቶች የመሩ እንጂ “ዲሞክራሲያ/ዲሞክራሲ” የሚባል እንዳልነበራቸዉ እኔ ባነበብኩት ታሪክ መከራከር እችላለሁ -ካሁን በፊትም በበቂ ማስረጃ ተከራክሬአለሁ። በዚህ ጥሪ ላቅርብ የሚከራከር ካለ ዝግጁ ነኝ! የኦሮሞ ህዘባችን በተፈጥሮ ዲሞክራት ሆኖ ከተፈጠረ ደስ ይለኛል እንጂ አይከፋኝም።ነገር ግን እኔ እና እኔን የወለዱኝ የትግራይ ወላጆቼ እና ቅድመ አያተቼ ፈጣሪያቸዉ ፈላጭ ቆራጭ ገዳዮች፤የስልጣን ጉግት እና ተሻሚ፤ፍትሕ አልባ _አዉቶሪተቲቭ ሆነዉ አልፈጠራቸዉም። ሆነዉ በተፈጥሮ እንዲያ ሆነዉ እንዲወለዱም አልፈልግም። ልዩነታችን ይሄ ነዉ። ህዝብን ማሳነስ ፤መዝለፍ እየተበራከተ እየሄደ ነዉ ስላችሁ አብዛኛኦቻችሁ “ቸል- በሉት” የሞኞች ንግግር ነዉ እያላችሁ እዚህ ድረስ ደርሰናል፦ እያደገ ሲሄድ እንደ እሳት ሰደድ ዘረኝነት ምን እንደሚያስከትል፤ ለናንተ ለብልህ አንባቢ አልነግርም።

ልጨርስ ነዉ-፤ በጣም አስፈላጊ እና አስገራሚ እና ሁላችንም አስተማሪ የሆነ ነገር ላስነብባችሁ እና ልሰናበታችሁ።

ከላይ በማስረጃ የነገርኳችሁ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሰርጎ ገቦች፤አስመሳዮች እንዲነቀቅ እና እኛኑን መስለዉ የተሰለፉበት ጸረ-ኢትዮጵያ ተልእኮአቸዉን ማክሸፍ ይጠበቅብናል። አንድነታችንም እየመነመነ የሄደዉ በሰርጎ ገብ ወኪሎቻቸዉ እንደሆነ እንወቅ። እኛን መስለዉ ጸረ- አንድነት የሆኑ ሃይሎች እንዴት እንደሚገቡ እና በሁለት ገጽታቸዉ ምን እንደሚመስል ለማስረጃ ከሰበሰብኳቸዉ የሚከተለዉን ማስረጃ ትምህርት እንዲሆነን የሚከተለዉ ደብዳቤ ለኔ የላከልኝን ጸረ- ኢትዮጵያ ኤርትራዊ ሰዉ “የትግራይ ተወላጅ” በመምሰል በመጀመሪያዉ ደብዳቤዉ እኔን “ምን እንዳለኝ” እና ከወር በሗላ ቆይቶ ደግሞ ኤርትራዊ ሆኖ በመቅረብ- የትግራይ ሰዉ በመምሰል ሲከላከልለት በስሙ ሲነግድበት የነበረዉን የትግራይን ሕዝብ ተምልሶ ምን ዓይነት ዘለፋ እንዳወረደበት ማስተማሪያ እንዲሆነን አንብቡት።

አነሆ_

From: henok kahsay <kahnoky@yahoo.com>
Subject: comment
To: getachre@sbcglobal.net
Date: Friday, December 5, 2008, 3:05 AM

Hey Getachew:

You see man, all the nasty paragraphs you write about this valiant, brave and capable people of TIGRAY simply tells how the memory of your defeat (EPRP’s defeat) at the hand of this same people is haunting you throughout your life. Poor Getachew. Yes, you were a big predicament on our struggle that has a clear and tenable strategy and end. So we had to kill you one by one in the battle. So we did that. Just bitter though it is take it. It is a reality. You were a curse to this country, so we had to get rid of you, man. So we did these in all the places you probably remember. Well I am sure you do remember each and every one of them. How can one forget places of defetas that have left an ever haunting effects. We had to fight and win you. We did this at Mereto, Bizet, and finally at your main place Asimba.

 As a result, we are enjoying everything at our threshold: everything from factory to companies, from transportation to agricultural products. Everything everything. there is nothing that we miss thanks to our struggle that beat you and EPRP.

 As to the complaint of the fighters at Guna after clearing Derg from Tigray, the organization, TPLF/EPRDF convinced the fighters and return them to their trenches to keep fighting. So what does this show? I think you must be a blockhead to miss the secret.It was simply because TPLF/EPRDF had the conviction that the whole Ethiopian people have to be freed from the yoke of the Derg. The organization had a broad based view and was not a rarrowist, as you wrote it in your Amharic text. So the bottom line is

WE WERE SUBJECTED TO EXTREME OPPRESSION AT THE HAND OF THE DERG

WE GOT ORGANIZED AND WENT TO DEDEBIT

WE GOT ARMED

WE FOUGHT

AND AS A RESULT, WE WON.

AND AS YOU SAID EVERYTHING IS AT OUR DISPOSAL (HULUM BEDEJACHIN, HULUM BEJACHIN)- min tameta err dibn bel

 

What do you say to this, Getachew ehapaw. 

Thenok kahsay” <kahnoky@yahoo.com>

: getachre@sbcglobal.net

hursday, December 11, 2008 1:48 AM

Now you started crying for the RED SEA.

Heyyyyy what abtih agebah sile Red Sea. It is Eritrean and only Eritrean property. Do not you know that we defeated you in 1991 and took our ports by force.

dedeb Agame

From: henok kahsay <kahnoky@yahoo.com>
Subject: comment
To: getachre@sbcglobal.net
Date: Sunday, September 7, 2008, 8:15 AM

Hello

You know every thing you write and post is really really silly, silly and non-sense. I think you too sound a big jilla jil. You must be one of the EPRP soldiers butted and badly beatten at Mereto and Asimba in 1971 E.C. The pain you suffered at that time in the hand of the gallant TPLF fighters does not seem to go out of your tormented mind. It will continue harrassing you until you give your last breath. That could be the reason why you are spending your time calling the name of weyane from dawn to dusk. Am I right, old man?

Henok, wedi weyane

–/- ———–//-

 

This entry was posted in Articles. Bookmark the permalink.

12 Responses to ለተከበራችሁ የኢትዮ ላዮን አሲምባ ደብተራዉ የህዋ ሰሌዳ አዘጋጆች የአስተዳደር ጥያቄ አቤቱታ።

Comments are closed.