Info

You are currently browsing the Assimba Blog weblog archives for the day 6. January 2009.

Calendar
January 2009
M T W T F S S
« Dec   Feb »
 1234
567891011
12131415161718
19202122232425
262728293031  
Categories
Links

Archive for 6. January 2009

እኔም ስለትብብር የምለው አለኝ


              ያትውልድ

ይህ አስተያየት እንድሰጥ ያነሳሳኝ አቶ ሲራክ ስለህብረት (ትብብር) ከ 1 እስከ 5 ያቀረበው አስተያየት ነው። በእርግጥ እኔም በከፊሉ እስማማለሁ። ቀሪው የማልስማማበት ሐሳቡ ላይ ግን ይህን አስተያየት ለመስጠት ተገድጃለሁ።

ወደ ህብረት ወይም ትብብር ጉዳይ ሀሳብ ከመስጠቴ በፊት እስኪ ስለ ትግሉና ትግል እናደርጋለን ስለሚሉ ድርጅቶች አላማ ልበል።

ላለፉት በተለየም 18 አመታት በጸረ ወያኔ ግንባር አያሌ የነጠላም የስብስብም ትግል ተካሂዶአል፤ በዚህ አውደ ውጊያ ብርቅ ድንቅ የሆኑ መልሰን ልናገኛቸው የማንችላቸው ነባር ታጋዮችን አጥተናል። ያም አሁን ላለው የተፋዘዘና እርስ በእርስ ያደበላለቀ ሁኔታ እንዲፈጠር አስተዋጸኦ አለው። በእርግጥ ነው ትግል በተናጠል ዛሬ ባለው ያገራችን ጭብጥ ሁኔታ የሚሆን ብንፈልግም የሚሳካ አይደለም በመሆኑም ይህችን አገር ከደመኛ ጠላታችን እጅ እንንጠቅ ካልን የድርጅቶች ማለትም ወያኔ ጠላት ነው መወገድ አለበት ብለው የሚያምኑ ሁሉ መስማማት ሲሆን መተባበር ካልሆነ ተከባብሮ ሳይጠላለፉ የጋራ ጠላት ላይ ማነጣጠር የሚጠበቅ ሁኔታው የሚያስገድደው ነው።

አቶ ሲራክ አምስት መስፈርቶች ለትብብር ወይም መፈጠር ላለበት ህብረት አቅርቦአል እነሱም 1-ያገሪቱን ሉአላዊነትና አንድነት የሚቀበሉ 2-እንደ AFD አይነት ጠላት ድርጅቶችን ያላቀፈ 3- ብቃት ያላቸው በግል መሬት የረገጡ መሆናቸው መታወቅ ያለበት 4- አስመሳይ ያልሆኑ 5- እወቁኝ ባይ ከሆኑ ለተክለ ሰውነት ከሚታገሉ መራቅ ይላል።

ከላይ ከሞላ ጎደል የተቀመጡት መስፈርቶች ያቶ ሲራክ ናቸው ታዲያ በእርግጥም ጠላት አንድ ብቻ ሳይሆን ጥንድ እንደሆነ ሊገጠም የሚገባውም በዚያው መልክ መሆኑን ይህ ጽሁፍ ያሳያል።

ጽሁፉ ውብ አቀራረብ እና መልካም እርእስ ከመያዙ በስተቀር እንደኔ አዲስ ነጻና ለየት ያለ እርእሱን የሚያግዝ ሀሳብ አልቀረበበትም ባይ ነኝ። ዛሬ በየፓልቶኩ ዘራፍ ሲባል የሚዋልበት ሀሳብ አልባ እና መረን ዘለል የሆኑ፤ ዛሬ ክበው ነገ ይሚያፈርሱ፤ ዛሬ አክብረው ነገ የሚያዋርዱ፤ ስለ ትግል ደንታ የሌላቸው ግለሰቦች ከዚህ የተለየ አላቀረቡም ያው እነሱ ሲሉት ሲደክሩበት የሚውሉትን ነው ሲራክም የደገመው። እንደኔ ሐሳብ ከሆነ ስለህብረት ወይም ስለትብብር ከማሰብ ከማለም በፊት ታጋይ ነኝ የሚል ግለሰብ፤ ስብስብ፤ ወይም ድርጅት ሁሉ የራሱን ህልም ተግባራዊ የሚያደርግበት ስልት ነድፎ ጠላትን በእውን የትግል አውድማ መፋለም መጀመር የግድ ይሆናል። ይህን ሳያደርግ ከተቀመጠበት ሳይነሳ ስለትብብር ማውራት ብቻውን ከወሬ ያለፈ አይሆንም። ተግባራዊ ቢሆን እንኩአን፤ የሚሰባሰቡት ያው መሰል ወረኞች ከመሆን ላይዘሉ ነው ባይ ነኝ።

ከላይ እንዳልሁት ዛሬ በየፓልቶኩ ስለ ትጥቅ ትግል ማውራት ወይም በትግል ስልት ልዩነት ፈጥሮ መነታረክ የተለመደ ሆኑአል። አንድ ጠበንጃ የተሸከመ ሰው ጫካ ሳይሰዱ ለምን ሰላማዊ ትግል አላችሁ ብለው ሲገለገሉ የሚውሉት ስንት ናቸው። የትናንት ቱባ ታጋዮች በስንቱ አፍ ተዘረጠጡ፤ ስንቱስ እነዚያን ብርቅየ ታጋዮችን አወገዘ? ያ ሁሉ የሚሆነው ዛሬ ባዲሱ ከኮምፒውተር ጀርባ ተቀምጦ በሚወራበት ፓልቶክ ነው። ዘንድሮም አምና ታች አምናም፤ እነዚያው ሰወች ስለትጥ፤ ስለህብረት፤ የጠላት አሰላለፍ ሲያወሩ ከርመዋል። ዛሬ ዛሬ አልፈው ተርፈው የዚህን የመነጋገሪያ መድረክ መቅለል ያዩ፤ መልከ መልካሞች የስደት መንግስት አዋጅ አውጀዋል። በነዚህ ሰወች መፍረድ የሚገባ አይመስለኝም። ስድቡንም ትናንት በታጋይነት ከሚያውቓቸው ዛሬ እርስ በእርስ ሲሰዳደቡ ያውም አይነት ያለው ስድብ ካፋቸው ሲወጣ አስተውለዋል። ባንድ አፍና ምላስ የስደት መንግስት ከመኝታ ክፍላቸው ሲያውጁ ከጥንት ታጋዮች መልስ ሲሰጥ ተመልክተዋል። እንግዲህ ያለንበትን ጊዜ ለማሳየት ስል የወዳጅ ጎራ የጠላት ጎራ ብሎ መከፋፈልም አስቸጋሪነቱን ለመጠቆም ነው ይኽን ያክል የምሽከረከረው። በእርግጥም አንድ ነገር መቀበል የግድ ይላል፡ ሁነኛ ታጋዮች ዛሬ እራሳቸው በፈጠሩት ችግር ተተብትበውና ተከፋፈለው ያሉበት ሁኔታ ነው የሚታየው። እንዴውም የዘመኑ በሽታ በነሱ የሚብስ ይመስላል። የነበራቸው ህብረተሰብን የመለወጥ ብርቅ ድንቅ ህልም ዛሬ በስድብና በመወነጃጀል ተለውጦ፤ ያጉል ተምሳሌ መሳለቂያ ለመሆን የቅድሚያ ቦታ ተይዞላቸዋል። ወደዋናው ጉዳይ ልመለስና፤ ላለፉት 18 አመታት ውብ ስራ የተሰሩትን ያክል ካንድ ህብረት ወደሌላ ሽግግር ግዜና ገንዘብ ያባከነ ይመስለኛል። ዛሬ ህብረት መፍጠር እንደዋነኛ የትግል ስልት በመቆጠሩ፤ በየትኛውም መታገያ እናምናለን የሚሉት ሜዳ ገብቶ ጠላትን ከመግጠም ይልቅ ከከተማ ከተማ መመላለስና ማን ከማን ይሆናል የሚለው ጎራ ልየታ በዋነኛነት በመያዙ ዋና ጠላት ተረስቶ፤ ፎክክሩ ቲፎዞ ማፍራት ሆኖአል። ይህ ለችግራችን አንዱ ይመስለኛል። ይህ ደግሞ ትንሽ ትልቅ ድርጅት ሳይለይ የተጠናወተን አቢይ ችግር ነው። አቶ ሲራክ እንዳለው AFD መቃወም መልካም ሆኖ ሳለ በምትኩ ግን ሊታይ ሊጨበጥ የሚችል ስራ ባለመደረጉ ካራት አመታት በሁአላም እዚያው ነን ማለት ነው። ዛሬ ስድብ ትግል፤ ትግልም ስድብ የሆነበት ጊዜ ነው። እንዴው ለላሙና ይህን የስድብ ጋጋታ ለማሳየት ከሁሉም በላይ አሳፋሪ ከሆኑት ትቂቶቹ “ እኔም ትግሬ ነኝ” በቤልጅግ አሊ “አለ ነገር በነብርቱካን መንደር” እነዚህን ለአብነት ለማሳየት እርእሶቹን ብቻ እንጅ ውስጠ ነገራቸው የሁለቱም ጽሁፎች አሳፋሪ አሳዛኝም እነዚያ ከጥንት ጀምረው ባረበኝነት በታገሉበት መድረክ ተራ የመንደር ተሳዳቢ ሲውረገረግበት ስናይ ባናዝን እናፍራለን ነው የሆነብን

እንግዲህ ህብረት ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ ቢኖር ኢዴሐቅ፤ አማራጭ ሐይሎች፤ ሕብረት፤ ቅንጅት ከነዚያ በፊትም ፓሪስ 1፤ ፓሪስ 2 የተባሉ ነበሩን ግና ምን ፈየዱ ብለን ዛሬ ሒሳብ ልናወራርድ ብንነሳ የምናገኘው አወ በየጊዜው አዳዲስ የህዝብ ተስፋ ሰጥተዋል፤ ብሎም ትግሉን ግን ለድል ማብቃት አልቻሉም የሚል የሂሳብ ዘገባ ይኖረናል ማለት ነው። ለህብረት ምስረታ የታገልነውን ያክል እያንዳንዱ ድርጅት ቀበቶውን ጠበቅ አርጎ እና ኮስተር ብሎ በመሰለው ቢታገል ኖሮ ምናልባትም ካለንበት የተሻለ ሁኔታወች ቢአንስ ይኖሩን ነበር አልያም በለስ ቀንቶን ጠላትን ፈንግለነው ነበር። እንዳለ እድል ሆኖ ግን ቪዥን ያለው ከራሱ በላይ ለህብረተሰብ ለውጥ በቁርጥ የቆሙ መሪወች እያነሱ ወይም እየጠፉ መሄዳቸው ነው ይመስለኛል። ዛሬ ላለፉት አራት አመታት ድርጅቶች ከውስጥ እየፈረሱ ከሌላው ጋር ስለመተባበር ሲያወሩ ከርመዋል። ትግሉም ከላይ እንዳስቀመጥሁት፤ ወይዛዝርቱ ሳይቀር ከቆንጆ ቤታቸው ሳይወጡ መታገልን ስላወቁበት የስደት መንግስት እስከማቆቓም ደረሱ ማለት ነው። በዚያ ተቃውሞ የለኝም። ማንም ሰው ያሰበውን መስራት መብቱ ነው። ደግሞም አማራጭ ነው ብለው ሲያቀርቡ መልካም ቸር መንገድ ከማለት የሚያልፍ ትርፍ የሚያናግር ነገር የለውም። ግን የነዚህ ዜጎች ይህን ያክል እረጅም መንገድ ማሰብ ምክንያቱ እንደማነኛችንም ተስፋ ማጣት እና ባሉ መሪወችና ድርጅቶች እምነት መመንመን ይመስለኛ። ለዚህ ያደረሰን ደግሞ አቶ ሲራክ በየፈርጁ ያስቀመጠው ከማን እናብር የሚለው በውነቱ እንኩአን አቀበት አንድ እርምጃ ቁልቁል የሚሄድ አይመስለኝም። ለምን? ለሱ ጠላት እንደሱ የማያስብ ሁሉ መሆኑ ነው። እነሱ አንጃ ይሉታል እሱም አጃ ይላል። ግን ቃሉ እራሱ ያለፈበት ስለሆነ በጀ ብሎ የሚያዳምጥ ባለመኖሩ፤ እንደኔ ከሆነ የቁራ ጩኸት ሆኖ የቀረ ይመስለኛል። በሚኒሊክ ጊዜ የደነቆረ ይባል አይደል። ዛሬ ዘፈኑም እስክስታውም ስለተቀየረ እንደ አቶ ሲራክ አይነቶች ሁሉ የከበሮውን አመታት ቢቀይሩ ይሻላል ሰሚ ለማግኘት ነው ዋናው ነገሬ።

ታዲያ የሲራክን አስተሳሰብ መንቀፌ መተባበር አያስፈልግም ለማለት ሳይሆን፤ 1- መተባበር አስፈላጊ ነው ግን ለትብብር ቅድመ ሁኔታ ተገቢ አይደለም 2- ዛሬ ጠላታችን አንድ ብቻ ሆኖ የዚህ ጠላት ጥንካሬ ደግሞ በተቃዋሚ ጎራ ያለው አለመስማማት በመሆኑ፤ እንደኔ ይህ መጭው ትግል መለኝነትን፤ መሰሪነትን የሚፈለግ ነው፤ ስለሆነም ማንም የዚህ ደመኛ ጠላትን መወገድ የሚያምን ሁሉ ከኦጋዴን እንስከ ኢሮብ፤ ከሰላማውያኑ ታጋዮች እስከ ታጣቂወች ቢቻል ባንድ የትብብር ጃንጥላ አልያም ላለመነካካት ተስማምቶና ተከባብሮ በጠላት ላይ ፊትን ማዞር ምርጫ የሌለው ነው ብየ አምናለሁ። ይህ ነው ከሲራክ ጋር የማያስማማኝ እንዴውም የሲራክ አስተሳሰብ የመሸበት እና ለጠላት ጠቃሚ በመሆኑ ደግሞ ይታሰብበት ባይ ነኝ።

ያትውልድ

|