የአቶ ሰውየውን ጽሑፎች በዚህና በሌሎችም ድረ-ገጾች ላይ ስለሚያገኟቸው ያንብቡና እኒህ ወገናችን
በሚሉት ላይ በመጨመር ወይም በመደገፍ ካለያም የግል አስተያየትዎን ያስቀምጡልን
አቶ ሰውየው ከሕብረተ-ሰቡ የሚሰነዘረውን ለመስማት ዝግጁ ነው።
ነገሬን በተረት ልቀድሰው ባገራችን አንድ አባባል አለ ይኸውም ሰውየው ማንን ታሸንፋለህ ቢሉት ሚስቴን አለ ይባላል ደካማነቷን አይቶ ማለት ነው እንደሱ ያለውንና የፈረጠመውን ጎረምሳ እንዳይል ፈርቶ ይህንን አባባል እኛም ዛሬ ኢሀደግን እየታገልን ነው የምንለውም የዚ ተረት ወራሽ ሆነን እንደ ወረርሽኝ በሽታ ተዛምቶብን ዋናውንና የሀገራችን ደመኛ እህአዴግን ከመታገል ይልቅ አቅም ያጣውንና ሊያገግምና ሊነሳ የሚጣጣረውን የህዝብ ወገን የሆነውን ድጋፍ የሚሻውን ደካማውን እየፈለጉ ጭራሽ ከበሽታው እንዳያገግም በተኛበት ሄዶ እንዳይነሳ ማድረግ ጀግንነት አድርገነው ደረታችንን እንነፋለን ይሄ ጀግንነት ወይም ወንድነት አይደለም ይልቁንም ይሄንን መሰል ድርጊት ፈጻሚውን ትንሽነትና እርካሽነት የሚያሳይ ጉልህ መስታወት ነው።
በቅርቡ በተደጋጋሚ በተለያዩ ድህረገጾች ላይ አቶ ሰውየው በሚል ስም የግለሰቦችን ስም እያነሳ በጣም የወረደና ዝቅ ባለ ክብረነክ ዘለፋዎችን ጽፎ ተመልክቼ በጣም አዝኛለሁ። እኚህ ሰው ብዙ ግዜ በምገባባቸው የውይይት መድረኮች ውስጥ እድል ገጥሞኝ ስገባ አደምጣቸው ስለነበርና አመለካከታቸውም ከኔ ከግል አመለካከት ጋር በብዙ መንገዱ ስለሚቀራረብ ለኚህ ሰው ትልቅ ከበሬታ ነበረኝ። አሁን ድርጅት በድርጅት ላይ እየተፈጠረ ተቃዋሚው ቡድን ከቀን ወደቀን እየደከመ እየተከፋፈለ በመጣበት ጊዜ በመሀከላችን ያለውን ልዩነት ለማጥበብና ለመሰባሰብ ጎንበስ ቀና እያልን በምንሯሯጥበት ወቅት ተቃዋሚ ነን በሚል ስም በአድራጎት ግን ኢሀዴግን ሊያግዝ የሚችል ነገር እየሰሩ ተቃዋሚውን ካለው ድክመት ላይ ይባስ የሚያዳክም የእርስ በርስ ሽኩቻን አጋኖና አልፎም ተፈጠረ ለሚባለው አለመግባባት እንዳይበርድ እያራገቡ ያለ የሌለ ነገር እየቀባጠሩ መዘባረቅ የሚያስተዛዝብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አለመግባባት ካለም ላለመግባባት ምክንያት ለሆነው ጊዜ ሰጥቶ ለችግሩ መፍትሄ መሻት በተገባ ነበር ያን ሳያደርጉ ተንደርድሮና ተቻኩሎ ነገሩ እንዳይበርድ ተጣድፎ ለነደደው እሳት ቤንዚን ማቀበል እጅግ የሚያሳዝን አቀራረብ ነው። ምነው እኚህ ግለሰብ ለተፈጠረው አለመግባባት አስታራቂ ሊሆን የሚችል ሀሳብ እንዳሁኑ ለመከፋፈልና ለማዳከም እንደሮጡት ለማስታረቁም በዚሁ ፍጥነትና ጉልበት አልሰሩበትም? ለማፍረስና ለመከፋፈል ሲሆን ምን አጣደፋቸው? ለግንባታ ሳይሆን ለማፍረሱ ብእራቸው ሰላ እነኚህ ተወቃሾች ዛሬ ቢያንስ ኢህአዴግን ባለ አቅማቸው እየታገሉ ያሉ ግለሰቦች እንደሆኑ እኔ እንደግለሰብ የምመሰክርላቸው ብቻ ሳይሆን ማንም ስራቸውንና ድርጊታቸውን ያየ ሁሉ የሚመሰክርላቸው ነው። ነገር ግን የህዝብ ወገን እንደሆኑ እያወቅን እኛ ያልነው ብቻ ካልሆነ እኛን ካላደመጡ በሚል ትምክህት ተነሳስቶ ይህን ያክል ወቀሳና ክብረነክ ባልተገባ ነበር ። ዛሬ ባለንበት አገር የኑሮውን ሁኔታ እያወቅን ያንን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለው እየታገሉ ያሉን ግለሰቦች እንደማበረታታት በተቃራኒው ከፍ ዝቅ እያደረጉ ማራከስና መዝለፍ ታጋዮች ከትግል እንዲርቁ ለማድረግ የሚደረግ የውስጥ ስራ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊሆን ይችላል ብሎ ለመገመት ያዳግታል።
ኢህአዴግን በጠላትነት የፈረጀና ኢህአዴግን እታገላለሁ ከሚል አንድ ግለሰብ የሚጠበቅም አይደለምና ጸሀፊው ያላቸው አቋም ኢሀዴጋዊ እንጂ ኢትዮጵያዊና ወገናዊ አልመስል ብሎኛል።
ይህንን ተደጋጋሚ የሆነ ጽሁፍ ሲያወጡ በነገሩ አላሰቡበትም አልተጨነቁበትም ለማለትም አያስደፍርም ስለሆነም የኚህን ግለሰብ የፖለቲካ አመለካከት ቀደም ብዬ አደምጣቸው ከነበረውና ከአንደበታቸው ይወጣ ከነበረው ቃል ጋር እጅግ የተለየ ሆኖ በማየቴ እውን እኚህ ግለሰብ ያን ሁሉ ጊዜ ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርገው ነበር የሚያቀርቡት? ያ ከሆነ በእውነት በማስመሰል ችሎታቸው ሳላደንቃቸው አላልፍም። ካልሆነ ግን መሰረተቢስ በሆነ የግል ፍላጎት ተነሳስቶ ዜጎችን ማዋረድ ባህላችን አይደለምና ጸሀፊው ልቦናው ሰጥቷቸው ወደህሊናቸው ተመልሰው ላደረጉት ስህተት ይቅርታ ጠይቀው ከትግሉ ጎራ ቢሰለፉ መልካም ነው የሚል አስተያየቴን እለግሳቸዋለሁ። ያን ማድረግ ቢያቅታቸው አንኳን ለሀገራቸው በሚደክሙና በሚለፉ ቡድኖችና ግለሰቦች መሀከል እየገቡ ቀና ሰዎችን እንዳይሰሩ ከማደናቀፍ ቢቆጠቡ ይመረጣል ይህንን መፈጸም ካልተቻላቸው ግን በትክክል ከየትኛው ወገን እንደሚያስፈርጃቸው ለጸሀፊው ልነግራቸው አይገባም ከኔ የላቁና ያወቁ ናቸው ብዬ አምናለሁና።
እዚህ ላይ አንድ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ጉዳይ ቢኖር እኚህ ግለሰብ የሚደግፉት ድርጅት የሚወነጀልበት አንዱ ጸሀፊው በጽሁፋቸው የሚያንጸባርቁት አይነት የእኔ አውቅልሀልሁና የሁሉ ነገር ፈጣረና ወሳኝ እኛ ብቻ ነን የሚል ትምክህተኝነት ስለሆነ የሚወነጀሉበትን ሁኔታ ያጠናክረዋልና ምናልባት የሚደግፉትና እየታገልኩለት ነው ለሚሉት ድርጅት እውነተኛ ደጋፊው ከሆኑ ለድርጅታቸው አሳቢና ተቆርቋረ ከሆኑ ድርጅቱን እየጎዱት እንጂ እየጠቀሙት እንዳልሆነ እንዴት ተሳናቸው? ድርጅቱም የጸሀፊው አካሄድ ትክክል እንዳልሆነ አስገንዝቦ አቋም ሊወስድበትና አባላቱንም እንዲታረሙ ማድረግ የሚቻልበት መንገድ ካለ በጽሞና ሊያስብበት ይገባል።
በትግል ስም ትግልን ማዳከም በኢትዮጵያዊነት ስም ኢትዮጵያን መግደል በህዝብ ስም ህዝብን መበደል ሊያበቃ ይገባልና ወደ ህሊናችን ተመልሰን አገራችን ከወደቀችበት አዘቅት እናውጣት።
አ . ሰመረ
አድርባይና አስመሳይ ታጋዮች ይጋለጡ
ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑር
አምላክ አገራችንን ይባርክልን
እኔም እስቲ በአበው ተረት ልጀምርና የአብዬን ወደ እምዬ ይሏል ይሄ ነው፡ አብዬ እውነትም አብዬ ለወያኔ ያጎነበሰው አንተና ጭራዎችህ ናችሁ ወይስ አቶ ስውየው? በጽሁፍህ የአንጃ አውራው ጋሽ ጥዑመ ልሳን እንደሆንክ የብዕር ስምህን እንኳን አይጋ ፎረም ላይ የአንጃነት አዶከበሬህ በጣም ባስገዘፈህ ወቅት ብቅ አድርገሃት አልሳካ ሲል ከወያኔው ድህረገጽ ጠፋህ ሰምህን እንኩአን የት እንደምትጠቀም ትረሳለህ የአልዛይመር ችግር እንዳለብህ ተረድቻለሁ፡ ኢህአዴግን ትላለህ ወያኔ ማለት ከብዶህ እንዲያው ከቶ ወያኔን ታግለህ ሞተሃል የወርድና የተዋረደ ሥራ እየሰራ ያለው አንተ ውይስ አቶ ሰውየው? የጓዶችህን ደም ረግጥህ የወጣህ አንተ ውይስ አቶ ሰውየው፡ ከዓለማቀፋዊነት ወደ ጎጥ ማሰባሰብ የወረድው፤እምነቱን ክዶ አፊዳቪትካልፈረምን ያልኩት ካልሆነ ብሎ በመዘረር ክብሩን ያጣው ማን ሆነና? በጣሙኑ ደግሞ የምያሳዝነው ትውልድ ከመተሩት ጋር አብሮ ቡሄ እየጨፈረ በኢትዮጵያዊነት ላይ የምያደቡትን አድናቂ ጋዜጠኛ ህኖ እያገለገለ ያለው ማን ሆነና? ለንዳንተ ዓይነቱ ውጉዝ ከመዓሪዎስ አስመሳይ ርካሽ ከሃዲ ይቅርታ የማይደረግለት ሥራ በመሥራትህ ከነጭራዎችህ መኮነን ሲያንስህ ነው፡ አቶ ሰውየው ለድንቅ ሥራውችህና ጥረቶችህ ብርታቱን ይስጥህ!!
ሰላም አቶ/ወ/ሮ /ሪት አ.ሰመረ
በመጀመሪያ ለተፃፉ ፅሁፎች መልስ ወይም የራሶትን ሃሳብ ለመሰጠት መነሳቶትን በጣም አደንቋለሁ ምክኒያቱም የሃሳቦች መሸራሸር ለትግላችን መጥራትና መጠናከር ይረዳልና. ሁለትኛ ደግሞ ፅሁፎቻችንና ሃሳቦቻችንን በራሳችን ሰም (አብዛኛውሰው ) በሚያወቀን ቢሆን ጥሩ ነው በተለይ ደገሞ አሰትያየት የሚሰጥበት ፅሁፍ ፀሃፊ በስማችው እሰከፃፉ ድርስ ማለት ነው ምክኒያቱም ያልሁኑ አሉባለታዎች ውሰጥ እንዳንግባና ሰዎችን ያላግባብ እነዳንወነጅል ይረዳናል ሌላው ደግሞ ሀሳቦቻችንና እምነታችን ይራሳችን እሰከሆነ ድረስ እራሳችንን መደበቅ በራሳችን ላይ አለመተማመን ይመስለኛል.(Call Me by my Name What is by my name) የሚለውን ፅሁፍ ፈልገው ቢያነቡ በራስ ስም የመጠራቱ ጥቅም ምን እነደሆን ትንሽ ሊረዱ ይችሉ ይሆናል.
ፀሃፊው ተብአት ከሆኑ,ከወነድ ትምክህተኛነት ራሳችውን ግና ያላላቀቁ ይመሰለኛል እንሰትም ከሆኑ እራሳችውን ነፃ ለማውጣት ከመታገል ይልቅ ከሌላው ያውም ከትምክተኛ ተብአት ድጋፍ(Sympath) ይጠይቃሉ.(ከፅሁፉ ምግቢያ ተረት(አባባል) በመነሳት)
አ.ሰመረ በፅሁፎት ላይ እነዲህ ይላሉ
አሁን ድርጅት በድርጅት ላይ እየተፈጠረ ተቃዋሚው ቡድን ከቀን ወደቀን እየደከመ እየተከፋፈለ በመጣበት ጊዜ በመሀከላችን ያለውን ልዩነት ለማጥበብና ለመሰባሰብ ጎንበስ ቀና እያልን በምንሯሯጥበት ወቅት ተቃዋሚ ነን በሚል ስም በአድራጎት ግን ኢሀዴግን ሊያግዝ የሚችል ነገር እየሰሩ ተቃዋሚውን ካለው ድክመት ላይ ይባስ የሚያዳክም የእርስ በርስ ሽኩቻን አጋኖና አልፎም ተፈጠረ ለሚባለው አለመግባባት እንዳይበርድ እያራገቡ ያለ የሌለ ነገር እየቀባጠሩ መዘባረቅ የሚያስተዛዝብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለመሆኑ ፀሃፊው ያሉትን
በነገራችን ላይ በወቅቱ ለሁለቱም ወገኖች መድረኮቻቸውን ዘግተው ችግራቸውን በውስጥ
እንዲጨርሱ ዶ/ር አበባ በከፈተችው መድረክ ላይም በመውጣት (ምንም እንኳ በጊዜው ዶ/ር
አበባ ብታስቆመኝም) ሃሳብ ካቀረቡት ወገኖች አንዱ ነበርኩ። እንዲያውም አንዳንድ ወንዶችና
የድርጅቱ አባላት ያልሆኑ ሴቶች ዶ/ር አበባ በከፈተችው መድረክ ላይ ወጥተው በጊዜው
በማያገባቸው ችግር ራሳቸውን ጥልቅ አድርገው የችግሩ መንስኤ ገነትና አስቴር ስለሆኑ መባረር
አለባቸው ብለው ሲደነፉ በነበረበት ወቅት ማለት ነው። አንብበውታል? ተደያ የቱ ላይ ነውያልውን ሽኩቻ ማጋንነ,አለመግባባት እነዳይበረደ እያራገቡ ይሚልውን ክስ ያመጡት?
ሌላ ቦታ ደግሞ እነዲህ ብልው ይፅፋሉ
ስለሆነም የኚህን ግለሰብ የፖለቲካ አመለካከት ቀደም ብዬ አደምጣቸው ከነበረውና ከአንደበታቸው ይወጣ ከነበረው ቃል ጋር እጅግ የተለየ ሆኖ በማየቴ እውን እኚህ ግለሰብ ያን ሁሉ ጊዜ ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርገው ነበር የሚያቀርቡት? ያ ከሆነ በእውነት በማስመሰል ችሎታቸው ሳላደንቃቸው አላልፍም።
የፀሃፊውን የ ፖልቲካ አመለካከት ይህ ነው ስላላሉን ምንም መናግር አልችልም ሆኖምግን ፀሃፊው ብዙ ጊዜ ሲናገሩ የሚዳመጡት ስለ ሕግ የበላይነትና ስለ ተጠያቂነትና ከ ግለሰቦች በፊት ለሃገራችንና ለሕዝባቸን ታማኘ አገልጋይ እንሁን ነወ በ ፅሁፋችውም ለይ ይማይውማንም መሪ ነኝ ባይ ከብዙኃኑ ድምፅ በልጦና ራሱን
ከድርጅት መተዳደሪያው ደንብ በላይ አድርጎ መቅረቡን ምንም ዓይነት ምክንያት ቢደረድር
በሕብረተ-ሰባችን ነውር መሆኑን መሪዎች ነን ለሚሉን ሁሉ ሊጥሱት የሚይገባቸውን መሥመር
አሥምረን በማስቀመጥ፤ በማናለብኝነትም ሲተላለፉ ቶሽ ብለን መንገዱን በማሳየትና
የድርጅታቸውን ዓላማ እንዳይረሱ ማስገንዘብ የእያንዳንዳችን ግዴታ ነው እላለሁ።
ይላሉ ፀሃፊው. ታዲያ ምኑ ላይ ነው ማሰመሰልያሉት?እዚህላይላቁም እነጂ ፅሁፎ በእውንት ክሁን በ አቶ ስውይው
ፅሁፍ ላይ በመመርኮዝ ሳይሆን ኩት አትብሉኝ የሹም ዶሮ አየንተ ሆኖ ንው ያገኘሁት ስድብ ይሏል ይህ ንው፡;የሚሉትን አንብቤ
የምልው ይኖራኛል፡;
አቶ ሰውየው ሲነሳ አሁን ከሆነ የሚግርመኝ ነገር ቢኖር 1-በ 79 ወቹ ከቆታጡመሪያችን ጋር ወደፊት ያሉት ባንዶች ናቸው። ሰሞኑን ለምን ትግሬ አላችሁ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ተስተውሎአል። ጉድ እና ጅራት እንዲሉ። አንዱ ያለቃው አሽከር እኔም ትግሬ ነኝ የሚል መጣጥፍ አስነበበን። እህ እኒህ ሰወች ወያኔ ወያኔ መሽተት ጀመሩ ያለኝ ጛደኛየ፤ ትግሬ ኦሮሞ ወይስ አማራ ወይስ ሁሉንም ዘር ያልተነካካ ኢትዮጵያዊ አለ እንዴ ያለኝ እውነትነት አሁን ከአእምሮየ አይጠፋም። ለመሆኑ ያማራ ትምክህተኝነትን እንታገል ሲባል አብሮ እንዳልደለቀ ሁሉ የትግሬ ጠባብነት አይኑን አፍጦ ባለባት ኢትዮጵያ ለምን ተንፍሳችሁ ማለቱ ማነን ለማስደሰት ይሆን? ከሁሉም የሚገርመው ከሀያ አመታት በላይ ፖለቲካ ለምኔ ብሎ የነበረው አቶ፣ ለዘመናት ከትግሉ ፈቀቅ ሳይሉ የታገሉትን ሲያክቸለችል ማየታችን ባያሳዝን አስገርሞናል።
የነገ ሰው ይበለን